ኮሚሽኑ የአርቲስት ሃጫሉን ግድያ ተከትሎ የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሪፖርት ይፋ አደረገ

66

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23 ቀን 2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ኮሚሽን የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል 40 ከተሞች የተፈፀመውን የሠብዓዊ መብት ጥሰት አስመልክቶ ያዘጋጀውን ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ኮሚሽነሩ ዶክተር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ ሌሎች ባለሙያዎች ሪፖርቱን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጡ ነው።

በከተሞቹ በተደረገው ዳሰሳ 30 ሙያተኞች መሳተፋቸው ተገልጿል።

የቀረበው ሪፖርት ከአርቲስቱ ግድያ ቀን ጀምሮ እስከ ሶስት ቀን የነበረውን ሁኔታ የዳሰሰ ነው።

በዳሰሳው ጉዳት ከደረሰባቸው የመንግስት አካላት ለ328 ሰዎች ቃለ መጠይቅ ተደርጓል፤ የፎቶግራፍ፣ የድምፅና ሌሎችም መረጃዎችና ማስረጃዎችም ተካተዋል።

በሪፖርቱ እንደቀረበው ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ንብረትም ወድሟል።

በዚህም 123 ሰዎች ተገድለዋል፤ 520 ሰዎች ደግሞ ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል።

በሰዎች ላይ በተለያዩ መሳሪያዎች አሰቃቂ ግድያ ተፈፅሟል ተብሏል በመግለጫው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም