በአሜሪካ የሚካሄደው የኢትዮጵያዊያን ጉባኤ አገራዊ አንድነትን እንደሚያጎለብት ተገለጸ

53
አዲስ አበባ ሀምሌ 14/2010 በአሜሪካ የሚደረገው የኢትዮጵያዊያን ህዝባዊ ጉባኤ አገራዊ አንድነቱን እንደሚያጎለብት ኢዜአ ያነጋገራቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናገሩ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው የልኡካን ቡድን ከሐምሌ 21 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ በአሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያን ጋር ውይይት ያካሂዳል። "የጥላቻና የልዩነት ግንብን አፍርሰን የፍቅርና የአንድነት ድልድይ እንገነባለን" በሚል መሪ ሃሳብ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ አባላት ጋር የሚካሄደውን ውይይት አስመልክቶ የምክር ቤቱ አባላት አስተያየታቸውን  ሰጥተዋል። አባላቱ እንዳሉት ውይይቱ ዲያስፖራው የአገሪቱን ኢኮኖሚ ከመደገፍ ባለፈ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ለማገዝ ሚናው ከፍተኛ ነው ያሉት የምክር ቤት አባል  አቶ ተስፋዬ አበራ ናቸው ፡፡ በአገር ልማትና እየታየ ባለው ለውጥ  የጋራ መግባባት ለመፍጠር ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ጋር የሚደረገው ድጋፍ ወሳኝ ነው የሚሉት ሌላኛው የምክር ቤት አባል ወይዘሮ ነኢማ አህመድ ናቸው። ሌላኛው የምክር ቤት አባል ወይዘሮ ቸርነት ኃይለማርያም በበኩላቸው ኢትዮጵያውያኑና ትውልደ ኢትዮጵዊ በአገራቸው ልማት ለመሳተፍ ያሳዩትን ተነሳሽነት ለማጠናከር መንግስት የጀመራቸው ስራዎች ውጤት እያስገኙ መሆኑን ተናግረዋል። በተደረገላቸው ጥሪ መሰረትም ወደ አገር ቤት በመምጣትና ባሉበት ሆነው ድጋፋቸውን የሚያሳዩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ መንግስት ይህንን ለማጠናከር የሚሰራውን ስራ እንደሚደግፉ ተናግረዋል። በተለይ በቴክኖሎጂና በዕውቀት ሽግግር፣ በአገራቸው ኢንቨስት በማድረግና የሌሎች አገሮች ኢንቨስተሮችን በመሳብ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማገዝ ያደረጉት ተነሳሽነት ሰፊ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም