የሠራዊቱ መነሻም መድረሻም ኢትዮጵያ ናት ... የመድፈኛ ሻለቃ አባላት

87

አዲስ አበባ፤ ህዳር 28/2013 የመከላከያ ሠራዊቱ መነሻና መድረሻ ኢትዮጵያ በመሆኗ ለሕልውናዋ መከበር በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን የመድፈኛ ሻለቃ አባላት ተናገሩ፡፡

ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የ11ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ብርጌድ 1ኛ የመድፈኛ ሻለቃ አባላት የህወሓትን ጁንታ እኩይ ድርጊት መክተው ድል እንደተቀዳጁ ሁሉ ለአገራቸው ሉዓላዊነት መከበር የድርሻቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

"የሠራዊቱ መነሻም መድረሻም ኢትዮጵያ ናት" ያሉት ሻምበል ባሻ አሰፋ ግርማ ሠራዊቱ አሁንም ወደፊትም "ለኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት በመሆንና ለሕገ መንግስቱ በመታመን ይሰራል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአገሩን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥና ዳር ድንበሯን ለማስከበር እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

ሻለቃ መጋቤ ባሻ ወልዴ ጣዲሶ በሰጡት አስተያየት የህወሓት የጥፋት ቡድን በሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ አባላትን በመጠቀም በሠራዊቱ ላይ የፈጸመው ክህደት ታሪክ ይቅር የማይለው ነው ሲሉ አስታውሰዋል፡፡

ለእኩይ ድርጊቱ ቀድሞ መዘጋጀቱንና በመሳሪያ ግምጃ ቤት የነበረውን መድፍ ቀድሞ በማበላሸት ሠራዊቱን ያለ ትጥቅ ለማስቀረትና ለማንበርከክ ሞክሮ እንደነበረም አውስተዋል፡፡

አባላቱ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉትም ጁንታው ህወሓት በሀገርና በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የፈጸመው ክህደት ታሪክ ይቅር የማይለው ነው ብለዋል፡፡

ሆኖም ሰራዊቱ ለሀገሩ ሲሰራ አይደክምም እና በጁንታው ላይ ድል ተቀዳጅቶ ለዚህ በመብቃቱም መደሰታቸውንም ገልጸዋል፡፡

በሰራዊቱ የ11ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ብርጌድ የ1ኛ የመድፈኛ ሻለቃ አባል የሆኑት ሻለቃ መጋቤ በሻ ወልዴ ጣዲሶ በሰጡት አስተያየት ቡድኑ በሰራዊቱ ውስጥ የሚገኙ የራሱን አባላት በመጠቀም ለእኩይ ድርጊቱ ቀድሞ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

በሰራዊቱ ንብረት ክፍል የነበረውን መድፍ ቀድሞ በማበላሸት እና ጥቅም እንዳይሰጥ በማድረግ ሰራዊቱን ያለ ትጥቅ በማስቀረት ለማንበርከክ ሞክሮ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

አመራሮችን የሚገድሉ የራሱን ሰዎች ከመመልመል አንስቶ በርካታ ዝግጅቶችን አድረጎ እኩይ ድረጊት ቢፈጽምም ሰራዊቱ በጀግንነት መክቶ ተዋጊዎቹን መደምሰሱን ገልጸዋል፡፡

ሻምበል ባሻ አሰፋ ግርማ በበኩላቸው ጁንታው ከጥቃቱ ቀደም ብሎ የራዲዮ መገናኛዎችን ወደ ራሱ በማዞር የሰራዊቱን ግንኙኘት አቋርጦ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ጁንታው በርካታ ነገሮችን ቢያደርግባቸውም የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር እና ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ እስከ ህይወት መስዋዕትነት ታግለው ድል መቀዳጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

የሠራዊቱ መነሻም መድረሻም ኢትዮጵያ ናት እና ለወደፊትም ለኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት በመሆን ለህገ መንግስቱ ታማኝ ሆነው የሚቀጥሉ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

ሰራዊት ለሀገሩ እስከ መስዋዕትነት ይሠራል ለወደፊትም ዳር ድንበሯን አስከብረው መስዋዕት ለመሆን ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

የ11ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ብርጌድ የ1ኛ የመድፈኛ ሻለቃ አባላት በተፈጸመባቸው ጥቃት ምክንያት ወደ ኤርትራ ተጉዘው ሀይል በማጠናከር እና ትጥቅ በማሟላት ወደ ሀገራቸው በመመለስ ጁንታውን ድል አድረገው በአሁኑ ጊዜ መቀሌን ከተቆጣጠሩት የሰራዊቱ አባላት መካከል ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊቱ እያደረገ ያለው ድጋፍናእያሳየ የላው አጋርነት ለሰራዊቱ ለሞራል ስንቅ እንደ ሆነው እና ሰራዊተቱ አንደ ሁል ጊዜው አገሩእና ህዝቡን የመጠበቅ ሃላፊተቱን ይቀጥላል ብለዋል የመድፈኛ ሻለቃ አባለቱ ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም