በአሶሳ ዞን ለመከላከያ ሠራዊት ከ3 ሚለዮን 4 መቶ ሺህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ተደረገ

71

አሶሳ ህዳር 25 ቀን 2013 ( ኢዜአ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ3 ሚለዮን 4 መቶ ሺህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብና ዓይነት ድጋፍ ተደረገ።

በዞኑ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ህዝባዊ ድጋፍ አሰባሰብ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ አረሺድ አጠይብ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ነዋሪዎቹ  ጁንታው ህወህት በሰሜን ዕዝ አባላት  ላይ ያደረሰው ጥቃት እጅግ አስቆጥቶታል፡፡

መንግሥት የህወሃትን ሃገር የማፍረስ ሴራ ለማክሸፍ በወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ በተገኘው ድል በመደሰት ህዝቡ ለሠራዊቱ ያለውን አጋርነት ለማሳየት ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

ለሠራዊቱ የተደረገው ድጋፍ በዞኑ ከሚገኙ የመንግስት ሠራተኞች፣ አርሶ አደሮች፣ ነጋዴዎች እና ከሌሎችም ተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በአጭር ጊዜ የተሰባሰበ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የጁንታው አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ለሕግ እስኪቀርቡ ድረስ ህብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ ለመቀጠል ቃል እንደገባ አስተባባሪው አመልክተዋል፡፡

ከድጋፉ መካከል በእጅ ከተሰጠው 400ሺህ ብር በተጨማሪ 97 ሠንጋ በሬዎች፣ 104 ሙክት በጎች እና ሃይላንድ ውሃ እንደሚገኝበት አቶ አረሺድ ተናግረዋል፡፡

እስከአሁን ከህዝቡ የተሰበሰበው አጠቃላይ ድጋፍ ከ3 ሚለዮን 400ሺህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብና ዓይነት  እንደሆነ አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡

የአሶሳ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኡስማን መሃመድ በበኩላቸው ፤ የዞኑ ህዝብ የህወሃት ቡድን በሰሜን ዕዝ አባላት ላይ በፈጸመውን ጥቃት ተቆጥቶ  ለሠራዊቱ የደጀንነት ድጋፍ ለማድረግ  መነሳሳቱን ተናግረዋል፡፡

ከድጋፉ በተጨማሪ ክልሉ ከሱዳን ጋር በሚዋሰንበት የአሶሳ ዞን የአስተዳደር ወሰን አካባቢ ህብረተሰቡ የነቃ ጥበቃ በማድረግ ሠራዊቱን እየደገፈ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም