የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ሠራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23/2013(ኢዜአ) የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ሠራተኞች በሕግ ማስከበር ስራ ላይ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ። 

ሰራተኞቹ የደም ልገሳውን ያከናወኑት ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብር ለመግለጽ “የሀገር ፍቅራችን በደማችን!” በሚል መሪ ሃሳብ ነው።


የቴአትር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አብዱልከሪም ጀማል ልገሳው ሠራዊቱን ለማክበር፣ ለማመስገንና እያበረከተ ላለው አስተዋፅኦ አጋርነታችንን ለማሳየት ነው ብለዋል።


በቀጣይም ሠራዊቱ ወዳለባቸው አካባቢዎች በመሄድ የተለያዩ ዝግጅቶችን ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።


ተዋናይ፣ ደራሲና አዘጋጅ ተሻለ ወርቁ ልገሳውን ያደረገው ሠራዊቱ እያከናወነ ያለውን ተግባር ለመደገፍና ለህብረተሰቡ አርአያ ሆኖ ለመገኘት እንደሆነ ገልጿል።


ድምፃዊ አሰግድ ስለሺም ለሠራዊቱ ደሙን በመለገሱ ደስታ አንደተሰማው ገልጿል። 


የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ኪነ-ጥበብን የአገር አንድነት ማስጠበቂያ ለማድረግ በ1927 ዓ.ም መቋቋሙን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም