በመቀሌ ከተማ የአገር መከላከያ ሰራዊት የማያውቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፓ ተገኘ

74

አዲስ አበባ፤ ህዳር 23/2013(ኢዜአ) በመቀሌ ከተማ የአገር መከላከያ ሰራዊት የማያውቀው የመሳሪያ ማከማቻ ዲፓ ተገኘ፡፡

የልዩ ዘመቻ 2ኛ ብርጌድ 3ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ሳድቅ አህመድ እንዳሉት በዲፖው ብሬንና ስናይፐርን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተከማችተው ተገኝተዋል።

ዲፖው በመከላከያ ሰራዊት የማይታወቅና በድብቅ የመሳሪያ ክምችት የተደረገበት መሆኑን ገልጸዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የመቀሌ ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎች አማካኝነት ወንጀል እንዳይፈጸም ጥብቅ ክትትል አያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በእስካሁኑ ሂደትም በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ለመንግስት ገቢ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪ በስፍራው የመገናኛ ሬዲዮዎች፣ መታወቂያዎችና የባንክ ደብተሮች መገኘታቸውን ተናግረዋል።

ይህም የጁንታው ቡድን አመራሮች ውጊያውን መቋቋም ሲሳናቸውው ትጥቃቸውን ጥለው መፈርጠጣቸውን  ያመላክታል ብለዋል።

አብዛኛዎቹ ሚኒሻዎች ደግሞ ተገደው እንዲዋጉ የተደረጉ በመሆኑ አጋጣሚውን ሲያገኙ ጥለውት ሄደው መሆኑን ጠቁመዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች እናቶች ጨምር ጥቆማ እየሰጡና የጦር መሳሪያዎችን በአቅራቢያቸው ላሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እያስረከቡ መሆኑን ሌተናል ኮሎኔል ሳድቅ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም