ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሎ የመከላከያ ሀይላችን ላጎናጸፈን ክብር መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ፤ ደስ አለን...ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

83

አዲስ አበባ፤ ህዳር 19/2013(ኢዜአ) ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሎ የመከላከያ ሀይላችን ላጎናጸፈን ክብር መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ፤ ደስ አለን ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ።

ህግ የማስከበሩ ምዕራፍ በድል ተጠናቋል ያሉት ፕሬዚዳንቷ፤ በመጪው ጊዜ ደግሞ ትልቅ ሥራ እንደሚጠብቀን ለአፍታም አንዘናጋ በማለት" እጅ ለእጅ ተያይዘን የሀገራችንን ልማትና እድገት ለማረጋገጥ ጠንክረን እንስራ" ነው ያሉት።

ከፕሬዚደንት ጽ/ቤት ማህበራዊ ገጽ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው "የአሁኑ የመከላከያ ሃይላችን ድል ለዚህ ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው፡፡ አኩርታችሁናል" ብለዋል ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ።

የመከላከያ ሠራዊቱ በትግራይ ክልል የህወሓት ጁንታ ቡድንን ለመቆጣጠር እያካሄደ ባለው ህግ የማስከበር እርምጃ መቀሌ ከተማን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም