በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ተጠናቋል_ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ

90

ህዳር 19 /2013 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ቀናት በትግራይ ክልል ሲካሄድ የነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን እና መቆሙን ላሳውቅ እወዳለሁ ብለዋል።

በመሆኑም በቀጣይ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ክልሉን መልሶ መገንባት እና ሰብአዊ ድጋፎችን ማድረስ መሆኑን በትዊተር ገፃቸው ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የፌደራል ፖሊስ በህግ የሚፈለጉ ወንጀለኛ የህወሃት አባላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እንደሚሰራም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም