ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ከጀርመን ቻንስለር የውጭና ደህንነት ፖሊሲ አማካሪ ጋር ተወያዩ

64

ህዳር 18/2013 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጀርመን ቻንስለር የውጭና ደህንነት ፖሊሲ አማካሪ ዶክተር ጃን ሄከር ጋር በርሊን ላይ ተገናኝተው ተወያዩ ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ገለፃ አድርገዋል ።

በዋናነት በትግራይ ክልል የተጀመረውን ህግ የማስከበር ዘመቻ አስመልክቶ የመንግሥትን አቋም ግልፅ አድርገዋል።

መንግሥት በሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ዙሪያ የጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ዓላማውን አብራርተዋል።

በህግ ማስከበር ሂደት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ አካላት ለአገልግሎት ምቹ እና ነፃ መንቀሳቀሻ ኮሪደር መመቻቸቱን ገልፀዋል።

በመጨረሻም የተጀመረው ህግ የማስከበር ዘመቻ በፍጥነት እንደሚጠናቀቅ ለአማካሪው እንዳረጋገጡላቸው ኢዜአ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም