በኢትዮጵያ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ በሚፈለገው ጥራት እና ፍጥነት ለማስቀጠል መንግሥት አስፈላጊውን ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል... አቶ ደመቀ መኮንን

78

ህዳር 17/2013 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ በሚፈለገው ጥራት እና ፍጥነት ለማስቀጠል ከሁለት ዓመታት በላይ መንግሥት አስፈላጊውን ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ መክረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአውሮፓ ሃገሮች የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ጉዟቸው ዛሬ በፈረንሳይ ቀጥሏል።

በኤሊዜ ቤተመንግሥት የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከውን መልዕክት ለፕሬዝዳንት ማክሮን አድርሰዋል።

በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ ጉዞ በሚፈለገው ጥራት እና ፍጥነት ለማስቀጠል ከሁለት ዓመታት በላይ መንግሥት አስፈላጊውን ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አቶ ደመቀ አስረድተዋል።

ይሁንና የህውሃት የጭጥፋት ቡድን የለውጥ ጉዞውን ለማደናቀፍ በህዝቡ እና በመንግሥት ላይ ተደጋጋሚ ጥፋቶችን ሲፈፅም እንደነበር አስታውሰዋል።

በመንግሥት በኩል ችግሩን በሰላም እና በውይይት ለመፍታት ተደጋጋሚ ጥረቶች ቢደረጉም፤ በአንፃሩ ቡድኑ እኩይ ድርጊቶችን መፈፀሙን አጠናክሮ እንደገፋበት ተናግረዋል።

በሂደት አስገዳጅ እና አሳዛኝ ድርጊቶች መፈጠራቸውን ተከትሎ መንግስት ህግ የማስከበር እርምጃ እየወሰደ የመጨረሻው ዘመቻ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንት ማክሮን በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት የውስጥ ጉዳዩን በራሱ ለመፍታት የሚያደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመጠቆም፤ ህግ በማስከበር እርምጃ ሂደት የንፁሀን ዜጎች ደህንነት ተገቢውን ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል።

በዘመቻው የአስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ መንግሥት የጀመረው ጥረት የሚበረታታ በመሆኑ፤ በቀጣይ ለተቀናጀ ሰብዓዊ እርዳታ አስቻይ መደላድሎች እንዲጠናከሩም ጠይቀዋል።

የኢትዮ-ፈረንሳይ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ከደረሱበት የትብብር ምዕራፍ በተሻለ ደረጃ ለማጠናከር መንግስታቸው ዝግጁ መሆኑን ፕሬዚዳንት ማክሮን ማረጋገጣቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮ-ፈረንሳይ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ከደረሱበት የትብብር ምዕራፍ በተሻለ ደረጃ ለማጠናከር መንግስታቸው ዝግጁ መሆኑን ፕሬዚዳንት ማክሮን ማረጋገጣቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Most Relevant

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም