የጌዴኦ ዞን ነዋሪዎች ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ህዳር 15/2013 (ኢዜአ) በደቡብ ክልል የጌዴኦ ዞን ነዋሪዎች ሕግ በማስከበር ዘመቻ ላይ ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሠራዊት ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ። 

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችም 400 ኩንታል ስኳር ለመከላከያ ሠራዊቱ አበርክተዋል። 

ከጌዴኦ ዞን የተወከሉ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የአገር ሽማግሌዎች የዞኑ ነዋሪዎች ያበረከተቱትን ድጋፍ በመከላከያ ሠራዊት ምድር ሃይል በመገኘት አስረክበዋል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽፈራው ቦጋለ ነዋሪዎቹ ከ9 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብና በዓይነት ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው 91 ሰንጋዎችና 35 በጎች ማበርከታቸውን ገልፀዋል፡፡ 

ይህ የመጀመሪያ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ድጋፉ ይቀጥላል ብለዋል።

የጌዴኦ የሀገር ሽማግሌ  ክህደት የፈጸመው ቡድን የእጁን አስከሚያገኝ ከመከላከያ ሠራዊት ጎን መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ 

መንግስት የጀመረውን ሕግ የማስከበር ስራ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡

በተመሣሣይ የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ የስራ ሃላፊዎችና ሠራተኞች 400 ኩንታል ስኳር ለአገር መከላከያ ሠራዊት አበርክተዋል።

ድጋፉን ያስረከቡት የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ካሳ ተስፋዬ የፋብሪካው ሠራተኞች የመከላከያ ሠራዊቱ የጀመረውን የሕግ ማስከበር ተግባር እስኪያጠናቅቅ ድረስ ከጎኑ ናቸው ብለዋል፡፡

የህወሓት ጁንታ በስኳር ኢንዱስትሪው ላይ ዘረፋ በማካሄድ ተወዳዳሪና ምርታማ እንዳይሆን ለበርካታ ዓመታት ማነቆ እነደነበረም ተናግረዋል፡፡

ቡድኑ በአገር ክህደትና በስኳር ኢንዱስትሪው ላይ በፈፀመው መጥፎ ተግባር ሕግ ፊት ቀርቦ እንዲዳኝ የፋብሪካው ሠራተኞች ምኞት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የአገር መከላከያ ሚኒስቴር የበጀትና ፕሮግራም ዳይሬክተር ብርጋዴል ጄኔራል አብዱሰላም ኢብራሂም ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል። 

መንገስት በትግራይ ክልል የሕግና የአገር ሉዓላዊነት የማስከበር እርምጃ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ኅብረተሰቡ ለአገር መከላከያ ሠራዊት ያለውን ድጋፍ በተለያየ መልኩ በመግለፅ ላይ ይገኛል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም