የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን "ከሀገር መከላከያ ጎን እንቆማለን" በሚል ለሰራዊቱ ያላትን ድጋፍ ገለጸች

880

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን "ከሀገር መከላከያ ጎን እንቆማለን" በሚል ለሰራዊቱ ያላትን ድጋፍ ገለጸች።

"ከሀገር መከላከያ ጎን እንቆማለን" በሚል መሪ ቃል የተላለፈውን ጥሪ በመቀበል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለመከላከያ ሰራዊቱ ያለውን ድጋፍና ክብር ገልጿል።

በመርሐ ግብሩ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በጸሎት የተከፈተ ሲሆን ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትም በመርሀ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል።

በመርሐግብሩ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከመከላከያ ጎን እንደሚቆሙ ማረጋገጣቸውንና ለሀገር ሰላምና አንድነትም የበኩላቸውን እንደሚያበረክቱ ቃል መግባታቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

"ለመከላከያ ክብር እቆማለሁ" በሚል መሪ ሃሳብ በኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የተዘጋጀው ይህ መርሐግብር በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተካሄደ ሲሆን የአገር መከላከያ ሠራዊት እየወሰደ ላለው የሕግ ማስከበርና የአገር ሕልውና የማስጠበቅ እርምጃ ድጋፍ ለመግለፅ ያለመ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም