ከሃዲ የሆነውን ጡት ነካሽ ኃይል ለማሳፈርና ለመደምሰስ አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን - ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ

አዲስ አበባ ጥቅምት 25/2013 (ኢዜአ) “ከሃዲ የሆነውን ጡት ነካሽ ኃይል ለማሳፈርና ለመደምሰስ አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ገለጹ።

ህወሃት በትግራይ የሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት በኮማንድ ፖስት እየተመራ አገሩን የማዳን ተልዕኮ እንዲወጣ የተሰጠውን ትዕዛዝ አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢቢሲ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም “ከሃዲ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን ወግተዋል፤ ኢትዮጵያ ባጎረሰ እጇ፣ ባጠባ እጇ ተነክሳለች” ብለዋል።

“ይህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ አሳዛኝ አሳፈሪም ተግባር ቢሆንም ዛሬም እንደተለመደው በተደመረና በተባበረ ክንድ ይህንን ከሃዲ ጡት ነካሽ ኃይል ለማሳፈርና ለመደምሰስ አስፈላጊውን ሁሉ የምናደርግ መሆኑን እገልፃለሁ” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም