የጎዴ ከተማን የልማት ማዕከል ለማድረግ የሚያስችሉ የመንገድ ፕሮጀክቶች ተጀመሩ - ኢዜአ አማርኛ
የጎዴ ከተማን የልማት ማዕከል ለማድረግ የሚያስችሉ የመንገድ ፕሮጀክቶች ተጀመሩ

ጥቅምት 19/2013(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሶማሌ ክልል የጎዴ ከተማን የልማት ማዕከል ለማድረግ እና የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችሉ የመንገድ ፕሮጀክቶችን አስጀመሩ።
ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የሚደረግባቸው እነዚህ ፕሮጀክቶች በ4 አመታት ውስጥ የሚጠናቀቁ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልፀዋል።

ዛሬ በሶማሌ ክልል ከ300 ኪ.ሜ. የሚበልጥ ርዝማኔ ያላቸውን መንገዶች ግንባታ አስጀምረዋል።
ከእነዚህም ውስጥ ከ270 ኪ.ሜ. በሚበልጥ ርዝማኔው የጎዴ -ቀላፎ ሎት -1 ፣ የጎዴ -ሐርጌሌ ሎት እና የያአሌ -ዳና ሎት -3 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ያካተተ ነው።
መንገዱ የአካባቢውን ነዋሪዎች ከማገናኘት ባሻገር፣ የጎዴ ከተማን የልማት ማዕከል ለማድረግና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።