አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለዶክተር ገብረአየሱስ ብርሀነ የሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕርግ ሰጠ

71

አክሱም ጥቅምት 18/2013 (ኢዜአ) አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዶክተር ገብረአየሱስ ብርሀነ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕርግ ሰጠ።

የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ትናንት ባዘጋጀው መድረክ ለዶክተር ገብረእየሱስ ብርሃነ የፕሮፌሰርነት ማዕርጉን አጽድቋል።

በዩኒቨርሲቲው የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽንና  አለም አቀፍ ግንኙነት  ዳይሬክተር   ተወካይ  አቶ ዳንኤል ዘሚካኤል ለኢዜአ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የፕሮፌርነት ማዕረጉን ሲሰጥ  ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ዶክተር ገብረእየሱስ በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ በአፈር እና ውሃ ጥበቃ ምህንድስና ዘርፈ ብዙ ጥናት ማድረጋቸው እና በግብርና ዘርፍ ባበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ  ቦርዱ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጣቸው ማጽደቁን አስታውቀዋል።

ፕሮፌሰሩ እስካሁን 34 ጥናታዊ ጽሁፎች በታወቁ አለም አቀፍ ጆርናሎች ማሳተማቸውን እና አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎች ማከናወናቸውም  ተመልክቷል።

ዶክተር ገብረእየሱስ  በቅርቡ  የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሆነው  መሾማቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም