በፌደራል የዳኝነት አስተዳደር እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጆች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው

53

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18/2013 ( ኢዜአ) በፌደራል የዳኝነት አስተዳደር እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጆች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው። 

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በረቂቅ አዋጆቹ ላይ ዛሬ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው።

በውይይቱም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

በአሁኑ ወቅት በፌዴራል የዳኝነት አስተዳደር ላይ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ለውይይት ቀርቧል።

ረቂቅ አዋጁ ስድስት ምዕራፎች እና 47 አንቀጾችን የያዘ መሆኑ ተገልጿል።

በቀጣይ አዋጁ ጸድቆ ወደ ሥራ ሲገባ የህግ የበላይነት እንዲከበር እና ፍርድ ቤቶች በህብረተሰቡ የተሻለ አመኔታ እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል።

በውይይት መድረኩ ላይ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ምላሽ ይሰጥባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም