ዲላ ዩኒቨርሲቲ 245 ተማሪዎችን አስመረቀ

46

ዲላ ጥቅምት 17/2013 (ኢዜአ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ በሕክምና ሙያ ያሰለጠናቸውን 245 ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቀ።

በምረቃ ሥነ ሥርዓት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍቃዱ ወልደማርያም እንዳሉት ከተመራቂዎቹ ውስጥ 28ቱ የህክምና ዶክተር ናቸው።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለያዩ የጤና መርሃ ግብር በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው ብለዋል።

ተመራቂዎች በቀሰሙት ሙያ ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን በታማኝነትና በቅንነት ከማገልገል ባለፈ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የድርሻቸውን እንዲወጡም   አሳስበዋል።

የእለቱ የማዕረግ ተመራቂ  ዶክተር አዱኛ አስፋ በሰለጠነበት ሙያ በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል በወሊድ ምክንያት የሚጎዱ እናቶችን ለመርዳት መዘጋጀቱን ተናግሯል።

ሌላኛዋ ተመራቂ ዶክተር ስምረት ተፈሪ በበኩሏ በተማረችበት ሙያ ክፍተት ባለበት አካባቢ በመመደብ  በቅንነት ለማገልገል ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።

በምረቃት ሥነ ሥረዓት አብላጫ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም