ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በደቡብ ወሎ ዞን በአንበጣ መንጋ የተጎዳ ሰብል እየጎበኙ ነው

94

ጥቅምት 15/2013 (ኢዜአ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የተመራ ልዑክ በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ በአንበጣ መንጋ የተጎዳ ሰብል እየጎበኙ ነው።

በጉብኝቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችም ተገኝተዋል።

አርሶ አደሩ ከመንግሰት ጋር ተቀናጅቶ የአንበጣ መንጋው የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ያደረገውን የመከላከል ጥረት ያደነቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ፤ ጉዳት ያጋጠማቸውን አርሶ አደሮች መንግስት የሚደግፍ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ዘጠኝ ሺህ ሄክታር የማሽላ ሰብል በማውደሙ አርሶ አደሩ ለችግር መጋለጡ ከዚህ በፊት የዞኑ ግብርና መምሪያ ለኢዜአ መግለጹ ይታወሳል።

የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ከቀላል ኬሚካል መርጫ እስከ አነስተኛ አውሮፕላን ድረስ በማሰማራት የኬሚካል ርጭት በማካሄድ ጥረት እየተደረገ ቆይቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም