በአፍሪካ የኮቪድ 19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ 5 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ታቅዷል

619

አዲስ አበባ ጥቅምት 13/2013 (ኢዜአ) አህጉሪቱ የኮቪድ 19 ክትባት ሲገኝ ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንድትሆንም ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል የበላይ ኃላፊ ጆን ነኬንጋሶንግ ለሮይተርስ እንደተናገሩት ባንኩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚዘጋጀውን ክትባት ለማዳረስ ድጋፉን ያሰባስባል፡፡

“ከአፍሪካ ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ ጋር ውይይት አድርገናል፣እነሱም 5 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ መዘጋጀታቸውን ገልጸውልናል ፣ በዚህም ተጨማሪ ክትባት ማግኘት እንችላለን” ብለዋል፡፡

አፍሪካ በፍጥነት ክትባቱን ለማግኘት በሚደረገው ውድድር ንቁ ተሳታፊ መሆን እንደሚጠበቅባት ተናግረዋል፡፡

በዓለም ጤና ድርጅት መሪነት ኮቫክስ የተሰኘ ጥምረት ዓለም አቀፍ በመፍጠር የኮቪድ 19 ክትባትን ለማዳረስ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም፤ከአህጉሪቱ 1 ነጥብ 29 ቢሊዮን ዜጎች መካከል 10 በመቶ ብቻ እንደሚሸፈን ገልጸዋል፡፡

ኮቫክስ ዋጋቸው አነስተኛ የሆነ የኮቪድ 19 ክትባትን በማምረት መንግሥታት ክትባቱን በብቸኝነት እንዳይቆጣጠሩት ለማድረግ የጀመረው ጥረት እኤአ እስከ 2021 ማብቂያ ሁለት ቢሊዮን ብልቃጥ ክትባት በመግዛት በፍትሃዊነት ለማሰራጨት ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ባለፈው ወር ለአፍሪካ 230 ሚሊዮን ብልቃጥ ክትባት ለማዳረስ ፍላጎት እንዳለው መግለጹን የተናገሩት ኃላፊው፣አቅርቦቱ እስከ 60 በመቶ የሚሆኑትን ዜጎች ስለማይሸፈን ተደራሽነቱ ውስን እንደሚሆን በመግለጽ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ኃላፊው እንደገለጹት ተቋማቸው ከህንዱ መድኃኒት አምራች ሴረም ኢንስቲትዩት ጋር በመነጋገር አስትራ ዜንካ ያበለጸገውን የኮቪድ 19 መከላከያ 200 ሚሊዮን ብልቃጥ ክትባት እንዲያመርት በመነጋገር ላይ እንደሚገኙ

ምዕራባውያን አገሮች በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በመመደብ ክትባቱን ለዜጎቻቸው በስፋት ተደራሽ ለማድረግ መንቀሳቀሳቸው ለአፍሪካ ፈተና ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡