በሐረሪ ክልል የተከሰተውን የቆዳ ማሳከክ በሽታ ለመከላከል እየተሰራ ነው

89
ሐረር ሐምሌ 9/2010 በሐረሪ ክልል የተከሰተውን የቆዳ ማሳከክ በሽታ ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ገለጸ። በቢሮው የህብረተሰብ ጤና፣ አደጋና ቁጥጥር ኃላፊ አቶ ቢኒያም ተሾመ ለኢዜአ እንደተናገሩት በሽታው ካለፈው ግንቦት ወር ጀምሮ በክልሉ አምስት ወረዳዎች ተከስቷል፡፡ በሽታውም እስካሁን 120 ሰዎች ተይዘው ተገቢው  የህክምና አገልግሎት እንደተደረገላቸው ተናግረዋል። ለጤና ተቋማትም መድሃኒት፣ ቅባትና ሳሙና የማሰራጨት ስራ መከናወኑን ጠቁመው ህብረተሰቡም የግልና የአካባቢን ንጽህና በመጠበቅ በሽታውን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ማገዝ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ የጅኔላ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ሰይፈዲን አሚን የጤና ጣቢያው የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በሽታውን ለመከላከል ቤት ለቤት በመሄድ ለህብረተሰቡ ትምህርት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም