በመዲናዋ ከነገ ጀምሮ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት እንደሚገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ   ጥቅምት 8 /2013 (ኢዜአ) በመዲናዋ ከነገ ጀምሮ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት እንደሚገቡ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት ችግር ለመቅርፍ ከነገ ጀምሮ 560 የግል ማህበራት አውቶብሶች በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ ተገልጿል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከግል የትራንስፖርት ማህበራት ጋር ስምምነት በማድረግ ነው አውቶብሶቹ በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ የተጠቆመው፡፡

በዛሬው እለትም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ የስምሪት ፕሮግራሙ ይፋ በመደረግ ላይ ነው።

ፕሮግራሙ በይፋ መጀመሩን አስመልክቶ ለከተማዋ ማህበረሰብ ከነገ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥም ተነግሯል።ዝርዝር መረጃው እንደደረሰን የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም