ሆስፒታሉ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የህክምና ቁሳቁሶች በድጋፍ አገኘ - ኢዜአ አማርኛ
ሆስፒታሉ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የህክምና ቁሳቁሶች በድጋፍ አገኘ
ሶዶ ጥቅምት 1/2013 (ኢዜአ) የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ቲችንግ ሪፈራል ሆስፒታል ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የህክምና ቁሳቁሶች በድጋፍ አገኘ።
ሆስፒታሉ ድጋፉን ያገኘው አዩዳ ኢን አክሲዮን ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው።
የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር ጌታሁን ሞላ ለኢዜአ እንደገለጹት ሆስፒታሉ የተደረገለት የቁሳቁስ ድጋፍ ለኮሮና ቫይረስ ህክምናና ለለይቶ ማቆያ የሚያገለግሉ ናቸው ።
ድጋፉ ሆስፒታሉ በዘርፉ እየሰጠ ላለው አገልግሎት የግብአት እጥረት ለማቃለል አስተዋጻ ያለው መሆኑን ተናግረዋል ።
የአዩዳ ኢን አክሲዮን የወላይታ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ፈለሃ በበኩላቸው ሆስፒታሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ፍጋፉ መደረጉን ተናግረዋል ።
ከቁሳቁስ ድጋፎቹ መካከል ለለይቶ ማቆያ የሚሆኑ 50 አልጋዎችና 15 የመተንፈሻ ማሽኖች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል ።
ድጋፉ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል ።