የትግራይ ወጣቶች በጸረ ድህነት ትግሉ ላይ እንዲረባረቡ ጥሪ ቀረበ

69
መቀሌ ግንቦት 5/2010 የትግራይ ወጣቶች የአካባበያቸውን ሰላም በመጠበቅ በፀረ-ድህነት ትግሉ ላይ እንዲረባረቡ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል  ጥሪ አቀረቡ። " ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ክልል አቀፍ የወጣቶች ኮንፍረስ ዛሬ በመቀሌ ሰማዕታት ሀውልት አዳራሽ  ተጀምሯል፡፡ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ኮንፍንሱ ሲጀመር ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቶች አሁን ያለውን ሰላም ፣ ልማትና  ዴሞክራሲ ማስጠበቅ እንዳለባቸው አመልክተዋል፡፡ የአካባበያቸውን ሰላም ጠብቀው  በፀረ-ድህነት ትግሉ ላይ በመረባረብ የራሳችውን ታሪክ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ነጋ አሰፋ በበኩላቸው የኮንፍረንሱ ተሳታፊ ወጣቶች  በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ በመወያየት ለመፍትሄውም ቁልፍ ሚናቸውን ሊጫወቱ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የክልሉ መንግስት ያዘጋጀውና ለሶስት ቀናት የሚቆየው የኮንፍረንሱ  ዓላማ የጥልቅ ተሀድሶው ሂደት ወደ ወጣቱም  በማውረድ ለተፈጻሚነቱ የድርሻውን እንዲወጣ ለማመቻቸት እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ በኮንፍረንሱ ከ2ሺህ በላይ ወጣቶች እየተሳተፉ ሲሆን እስካሁን በተከናወኑና በተመዘገቡ ውጤቶች የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ ውይይት እንደሚደረግ ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም