ለፕሬዝዳንት ኢሳይያስ የተደረገው አቀባበል የህዝብ ለህዝብ ወዳጅነት እውን እንዲሆን ያለውን ፍላጎት ያሳያል - ነዋሪዎች

116
አዲስ አበባ ሐምሌ 7/2010 ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የተደረገው አቀባበል በሁለቱ አገራት ህዝቦች መካከል ጠንካራ ወዳጅነት እውን እንዲሆን ያለውን ፍላጎት የሚያሳይ ነው በማለት ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ። የአቀባበል ስነ-ሰርዓቱ የሁለቱ  አገራት ህዝቦች በመካከላቸው ፍቅርና አንድነት ይመጣ ዘንድ ለረጅም ዓመታት መናፈቃቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎቹ ገልፀዋል። የአቀባበል ስነ-ስርዓቱ የኢትዮጵያዊያንን እንግዳ ተቀባይነት ከማንፀባረቅ ባሻገር ከኤርትራዊያን ወንድምና እህት ህዝብ ጋር ጠንካራ ሁለንተናዊ የትብብር ግንኙነት እንዲፈጠር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በአገራቱ መካከል የተጀመረው መልካም ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ኃላፊነት እንዳለበት ነው አስተያየት ሰጪዎቹ የተናገሩት። አቶ መኮንን ኃይሉ በፊትም የተለያየ ህዝብ አልነበርንም ዳግም ያንን አንድንት ያሳየንበት ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረው፤ ኢትዮጵያውያን ጨዋዎችና እንግዳ ተቀባዮች በመሆናችን ጥሩ መስተንግዶ እያደረግን እንደሆነ ይሰማኛል ብለዋል፡፡ አቶ እንዳልካቸው ተሾመ እንደገለጹት “በእውነቱ ከሆነ ይህ ህዝብ ፍቅርን፣ ሰላምን፣ ዕድገትን፣ ሁሌም የሚመኘው ነገር ሲናፍቀው ሁሌም ሲኖር ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኤርትራ መጥተዋል፤ ከዚህ ቦኃላ አንድ በመሆን እንኖራለን፡፡ ወጣት ጌታቸው አርባ  የህዝቡ አቀባበል ባለፈው ኤርትራ ላይ አቀባበለቸውን አይተን ተገርመን ነበር፤ እኛም እጅግ በጣም ስንጠብቀው የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ  በከፍተኛ ድስታ ሊንቀበል ተስፋ እድረግን ስንጠብቀውም የነበረው በመሳካቱ በጣም ድሰ ብሎናል"። ብሏል፡፡ ወይዘሮ ገነት ታደሰ "እኔ በበኩሌ በጣም በጣም ተደስቻለሁ፤ ህዝቡም በጣም ደስ ይላል፤ ከ20 ዓመት በፊት አስመራ ነበርኩ ከባድ ግፍ ይፈጸም ነበር፤ በአሁኑ ወቅት ፍቅርና ሰላም በመኖሩ የህሊና እረፍት አግተናል”          ኑው ያለችው፡፡  ያለጦርነት የፍቅር አምላክ ነው ይህ መሪ ያመጣልን በምድራችን ላይ በመሆኑና ፕሬዝዳንት ኢሳያስም በሰላም በመምጣታቸው ደስ ብሎኛል፤ ደስታዬን እንዴት እንደምገልጸው አላውቅም፤ ህዝቡም ላይ የሚታየው ሰላምና በጣም የተረጋጋ ደስተኛ ነው መሆኑንም ተናግራለች፡፡ አቀባበሉ በጣም ደስ ይላል ከብዙ ዓመታት  ናፍቆት በኋላ የተገናኘነው፤ ቀድሞም መለያየታን አስፈላጊ አልነበረም ፤አሁን ግን አንድ የሚያደርገን  በመምጣቱ መንገዱን አሳምሮ በመሄድ በአንድነት ተሳስበን፤ ተፋቅረን ተከባብረን እንኖራለን"ያሉት ደግሞ አቶ ዮሐንስ ንጉሴ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም