ፈተና የበዛባቸው ሀገራዊ እሴቶቻችን ልንጠብቃቸው ይገባል

50

 አዲስ አበባ  መስከረም 19/2012 ( ኢዜአ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፈተና የተጋረጠባቸው ሀገራዊ እሴቶችን     ልንጠብቃቸው አንደሚገባ ተጠቆመ ፡፡

ከሚለያዩን ነገሮች ይልቅ አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ በማተኮር መቻቻልን   ማስቀደም ያስፈልጋል ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የተለያዩ የህብረተሰብ  ክፍሎች ገለጹ፡፡

ትህትና ና ፍቅርን  በማስቀደም   ለትውልድ ምቹ ሀገርን ማስረከብ  የሁሉችንም  ሃላፊነት ነው የሚሉት የአንቀፀ ምህረት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስትያን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ምህረት መምህር ቃለ ፅድቅ ከፍያለው ናቸው፡፡

በሰላም፣በፍቅርና በአንድነት ተከባብሮ  መኖር  ለድርድር የሚቀርብ  ባለመሆኑ  ሰላማዊና የተረጋጋች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ  ብዙ ስራ እንደሚጠይቅም  ጠቁመዋል፡፡

ወጣቶች  በጥርጣሬና በጥላቻ  መተያየት  የትም እንደማያደርስ ተገንዝበው ከታላላቆቻቸው የወረሱትን የጋራ እሴቶች  ማስቀጠል አማራጭ የለውም ያሉት ደግሞ መጋቢ ሃዲስ ዳኒኤል ወ/ገሪማ ናቸው፡፡

የሰው ልጅ በሰውነቱ እንጂ በብሄሩ አለያም በሃይማኖቱ ሊገለልና ጥቃት ሊደርስበት እንደማይገባ ጠቅሰው መከባበርና ፍቅርን  ማስቀደም ለአንድነትታችን መሰረት   መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ወጣት ቢኒያም ዮሴፍ በበኩሉ  አንድነት ሃይል  በመሆኑ  እንደ ሃገር  በመደማመጥና  በመከባበር ልዩነቶቻችን መፍታት አለብን ይላል፡፡

የአባቶቻችን ጣልያንን የማሸነፋቸው ሚስጢር  በአገር ወዳድነት በጋራ መሰለፋቸውን ነው የሚለን   ወጣት ቢኒያም  አንድነታችንን ሊሸራርፉ የሚጥሩ  አካላትን ማስቆም አለብን  ብሏል ፡፡

 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሚስተዋለው መጥፎ ባህሪ   ልጆቻቸው እንዲቆጠቡ ማስተማራቸውን የሚነግሩን ወሮ ሰብለ ጥላሁን        ወላጆች የልጆችን ውሎና ስነ ምግባር  በመከታተልና መምከር እንዳለባቸው   በመጠቆም ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም