በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ንብረታቸውን ላጡ አሰሪዎች የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተጀመረ

60

አዲስ አበባ  መስከረም 18/2012 ( ኢዜአ) በወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት ንብረታቸውን ላጡ አሰሪዎች የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል።

"አሰሪው ለአሰሪው" በሚል መሪ ሀሳብ ማምሻውን በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል እየተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተጀምሯል።

መርሃ ግብሩ የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተከትሎ በተፈጠረ ሁከት ንብረታቸው ለወደመባቸው በአይነትና በገንዘብ ማሰባሰብ አላማ ያደረገ ነው።

በምሽቱ መርሃ ግብር ግማሽ ቢሊዮን ብር በአይነትና በገንዘብ በማሰባሰብ ለአሰሪዎችና ለሰራተኞች ለማከፋፋል እቅድ ተይዟል።

የተሰበሰብውን ሃብት በፍትሐዊነት የሚከፋፋል መሆኑም ተገልጿል።

ለዚህም አገር አቀፍ አስተባባሪ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራ ነው።

በተከሰተው ችግር ምክንያት ስራቸውን ያጡ ሰራተኞች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ማድረግ እንድሁም የጎላ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዳለው በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የሰራተኛና ማህባራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት (አይ ኤል ኦ) የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም