ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ለመቆጣጠር ህብረተሰቡ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተመለከተ

93

ሠመራ መስከረም 14/2013 (ኢዜአ) ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር  ለመቆጣጠር ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሆን የድርሻውን መወጣት እንዳለበት ተመለከተ።

አዲሶቹ የብር ኖቶች  ቅያሬ ዛሬ በአፋር ክልል በይፋ በተጀመረበት ወቅት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ  እንደተናገሩት  ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ከተራ ስርቆት በላይ የሀገርን ህልውናና የህዝብን ደህንነት የሚፈታተን አደገኛ ወንጀል እየሆነ መጥቷል

ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የኢኮኖሚ አሻጥር በመፍጠር አላስፈላጊ የዋጋ ንረት እንዲሁም ገንዘብ የመግዛት አቅም እንዲዳከም እያደረገ ነው ብለዋል።

የብር ኖቶች ለውጥ መደረጉ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ወሳኝና አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም  የገንዘብ ለውጡ  ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን፣ የአርብቶ አደሩን ባህልና ወግ እውቅና የሰጠ  መሆኑንም አመልክተዋል።

ይህም  መልካም እድል ይዞ የመጣውን የብር ኖት ለውጥ  በህገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪዎችና ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች እንዳይደናቀፍ የክልሉ መንግስት ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት  ጋር እየሰራ  መሆኑን አሰታውቀዋል።

ቁጥጥሩ በአንድ አካል ብቻ  የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣ ስለማይችል የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር  ሽማግሌዎችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች  ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ለመግታት ከመንግስት ጎን በመሆን  የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሠመራ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አወል መሐመድ በበኩላቸው አዲሶቹ የብር ኖቶች በሁሉም የንግድ ባንክ ለማድረስ ከክልሉ የጸጥታ መዋቅር ጋር በመሆን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በቂ የብር ኖት በመኖሩ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ ያለምንም መጨናነቅ መቀየር የሚችለበት ሁኔታ መመቻቸቱንም አስታውቀዋል።

የሱማሌክልልርዕሰመስተዳድርአቶሙስጠፌመሃመድኡመርኡጋዞችንናገራዶችንእንዲሁምየተለያዩየሃይማኖትአባቶችእንዱሁምልዩ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም