የወለጋ ዩኒቨርሲቲ 3 ሺህ 608 ተማሪዎችን አስመረቀ

110

ነቀምቴ መስከረም 14/2013 (ኢዜአ) - የወለጋ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በተከታታይና በርቀት መርሀ ግብር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 608 ተማሪዎች ዛሬ አስመረቀ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀሰን ዩሱፍ በምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ እንደገለጹት ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል ስምንቱ በሦስተኛ፣ 1 ሺህ 153ቱ  በሁለተኛና ቀሪዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ የተሰጣቸውን ትምህርት ያጠናቀቁ ናቸው።

ተማሪዎቹ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተሰጣቸውን ሥልጠና በአግባቡ በማጠናቀቃቸው ለምረቃ መብቃታቸውን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ አራት ተማሪዎችን በአፋን ኦሮሞ በሦስተኛ ዲግሪ ማስመረቁ የዘንድሮውን ሥነ ሥርዓት ልዩ እንደሚያደርገው ጠቅሰዋል።

በአፋን ኦሮሞ በሦስተኛ ዲግሪ ተመራቂ ዶክተር ዳንዔል ለሜሳ ለምረቃ በመብቃቱ ደስተኛ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ ለቋንቋው ዕድገት የሚረዱ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ለመካሄድ ዓላማ ማድረጉን ገልጿል።

"በተመረኩበት የሙያ መስክ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት የድርሻዬን እወጣለሁ" ያሉት ደግሞ ሌላው በአፋን ኦሮሞ በሦስተኛ ዲግሪ የተመረቁት ዶክተር መገርሣ ዲንሣ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም