ቦትስዋና ሚስቶችን የመሬት ባለቤት የሚያደርግ የህግ ረቂቅ ይፋ አደረገች

69

መስከረም 8/2013(ኢዜአ) ቦትስዋና ሚስቶችን የመሬትባለቤት የሚያደርግ አዲስ የህግ ረቂቅ ይፋ ማድረገጓን ፕሬዘዳንት ሞክግወትሲ ማሲሲ ገልጸዋል።

እንደ  ፕሬዘዳንቱ ገለጻ አዲስ ይፋ የተደረገው  ህግ ሚስቶችን ከመጋባታቸው በፊት በባሎቻቸው ተይዞ ከነበረው ንብረት ባለ ሙሉ መብት የሚያደርግ ነው።

እ.አ.አ አቆጣጠር በ 2015 ወጥቶ የነበረው የሀገሪቱ ህግ በተለይ የሚስቶችን የንብረት ባለቤትነት መብት የሚያረጋግጥ አልነበረም።

ፕሬዘዳንት ሞክግወትሲ ማሲሲ ̎የ2015 የሀገሪቱ የመሬት ፖሊሲ ሴቶችንና ወንዶችን እኩል የሚያስተናግድ አልነበረም፣ባገቡ ሴቶች ላይ ከፍተኛ ጫና ነበረው፣አሁን ግን ይህን አድሏዊ አሰራር የሚሽር  አዲስ ህግ ይፋ ተደርጓል በዚህ ደግሞ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል̎  ብለዋል በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባደረጉት ንግግር።

አድሎው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ያገቡ ሴቶችን ፣ ከባሎቻቸው ጋር በፍቺ የተለዩ ሴቶችንና ነጠላ እናቶችን የመኖሪያና የመስሪያና ቦታ ያሳጣ ነበር ነው ያሉት ፕሬዘዳንቱ።

ሴቶች የመሬትን ባለቤት ለመሆን በርካታ  መሰናክሎች ያጋጥሟቸዋል።

እንደ አለም አቀፉ የመሬት ባለቤትነት መብት ድርጅት ገለጻ ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ የአፍሪካ እና የእስያ አርሶ አደሮች ሴቶች ቢሆኑም ከአጠቃላይ የእርሻ መሬት ውስጥ ግን 15 በመቶው ብቻ ነው በሴቶች የተያው ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም