የጤና ሚኒስቴር ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ አገራዊ ምርጫ ማካሄድ እንደሚቻል ምክረ ሀሳብ አቀረበ

66

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8/2012(ኢዜአ) በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው አገራዊ ምርጫ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ማካሄድ እንደሚቻል የጤና ሚኒስቴር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ምክረ ሀሳብ አቀረበ።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

የማስክ መጠቀምና ሌሎች የቫይረሱን መከላከያ መንገዶች ዙሪያ የህብረተሰቡ ግንዛቤ መሻሻል፣ በቂ የመከላከያ ግብዓቶች መኖራቸው እና ዘርፈ ብዙ ምላሽ የመስጠት አቅም ማደጉ እንዲሁም የሀገራትን ምርጫ ተሞክሮ በማየት የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን በማሟላት ሀገራዊ ምርጫውን ማካሄድ እንደሚቻል የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል።

ለምሳሌ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ምርጫ ሂደት በተለየ መልኩ ኮቪድ- 19ን መከላከልን ከግምት ውስጥ በማስገባት የምርጫ ስነ ምግባር ደንብና የማስፈጸሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀትና በተዘጋጁት ዝርዝሮች መሰረት በበቂ ዝግጅት ወደ ተግባር መግባት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በዚህ ሂደት ውስጥ በአንዳድ ቦታዎች ላይ የወረርሽኝ ስርጭት ከተከሰተ በተለየ ሁኔታ ማየት ሊያስፈልገው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት ያስፈልጋም ብለዋል።

በሀገራችን ወረርሽኙን በተመለከተ ቀደሞ ከነበሩ ትንበያዎች አንጻር ከፍተኛ አለመሆኑ ኮቪድ -19 ረዘም ላለ ጊዜ አብሮን ሊቆይ መቻሉ እና በአንጻራዊ ምርጫው ሲካሄድ ከነበርንበት ሁኔታ በሽታውን ለመከላከል በቂ መረጃ መኖሩ፣ ማስክ፣ ንፅህና እና መራራቅ የመሳሰሉ በሽታውን ለመከላከል የሚረዱ ሳይንሳዊ መረጃዎች በከፍተኛ ደረጃ ስርጭቱን ለመከላከል እንደሚያግዙ መታወቁ ለምርጫው ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚችል አብራርተዋል።

በኮቪድ- 19 ምክንያት የተለያዩ ሀገራት ምርጫን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ ያራዘሙ ሲሆን አንዳንድ ሀገራት ምርጫዎቻቸውን ቀድሞ በተያዘለት ጊዜ መሰረት አከናውነዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም