የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር የልማት ስትራቴጂና የጭነት አገልግሎትን ለማስተዋወቅ ያለመ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

416

 አዲስ አበባ መስከረም  7/2013 (ኢዜአ) የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር የልማት ስትራቴጂና የጭነት አገልግሎትን ለማስተዋወቅ ያለመ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

ፉሪ – ለቡ በሚገኘው የባቡር ጣቢያው እየተካሄደ ባለው በእዚሀ ጉባኤው የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂያን እና ሌሎች የቻይና ድርጅት ተወካዮች ታድመዋል። 

አገልግሎቱን በጥር ወር 2010 ዓ.ም በይፋ የጀመረው ኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ኢትዮጵያና ጅቡቲን ማስተሳሰሩንና እስካሁን ድረስም ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ቶን በላይ የወጭና ገቢ ጭነት ማጓጓዙን የድርጀቱ ዋና ዳይሬከተር አቶ ጥላሁን ሳርካ ገልፀዋል። 

የባቡር መስመሩን በገነቡትና በኦፕሬሽን ሥራዎች ላይ ከሚሳተፉ ቻይና በቀል ድርጅቶችም የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሸግግር መካሄዱን ነው የተናገሩት። 

የባቡር መስመሩ ለኢትዮጵያ ብልፅግና ጉዞ መልካም ተስፋ እንዳለውም በጉባኤው ላይ ተመልክቷል።