የባሕር በር አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት መድረክ በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው 

125

ሮቤ ፤ ሚያዚያ 15/2016(ኢዜአ)፡- "የባሕር መውጫና ኢትዮጵያ " በሚል መሪ ሃሳብ  የባሕር በር አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት መድረክ በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

በዚህም  የኢትዮጵያ የባህር በር አጠቃቀም ጉዳይ፣ ቀጣናዊ ትስስርና ለዘላቂ ሰላም ያለው ፋይዳ ላይ የተኮሩ ጥናታዊ ጽሁፎች  ቀርበው በታዳሚዎች ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።  

በውይይቱም  ምሁራንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ። 

ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት የሚያስችላትን የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሌላንድ ጋር መፈራረሟ ይታወሳል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም