ኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ ላይ ያላት አቋም ዛሬም የጸና ነው - አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር)

465

አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2016 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ ላይ ያላት አቋም ዛሬም የጸና መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚስኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ገለጹ።

አምባሳደር መለስ ዓለም ለኢዜአ እንደገለጹት ኢትዮጵያ የአንዲት ቻይና ፖሊሲን ለረጅም ዓመታት ስታራምድ ቆይታለች።

የኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋም በዘመናት መካከል መንግስታት አፅንተው የያዙት አቋም መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ ላይ ያላት አቋም ዛሬም የጸና መሆኑን ተናግረዋል።
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም