ቀጥታ፡

ምክር ቤቱ የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ

አዲስ አበባ፤ሰኔ 2/2018 (ኢዜአ)፦የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን እና የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጽድቋል።


 

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።


 

በዚህም የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።


 

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም