በልዩ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የጠቅላላ ምርጫ የድምጽ መስጠት ሂደት - ኢዜአ አማርኛ
በልዩ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የጠቅላላ ምርጫ የድምጽ መስጠት ሂደት
አዲስ አበባ ፤ ሰኔ 2/2018 (ኢዜአ)፦በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና በወታደራዊ ካምፖች በሚገኙ ልዩ ጣቢያዎች በልዩ ሁኔታ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጠት ሂደት እየተከናወነ ይገኛል።
ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማስፈጸሙ ይታወቃል።
በተጨማሪም ቦርዱ “በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 17” በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና በወታደራዊ ካምፖች ልዩ ጣቢያዎችን በማቋቋም የካምፑ ነዋሪዎችን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ እንዲሣተፉ በመራጭነት መመዝገቡ ይታወቃል።
በዚሁ መሰረት በካምፖቹ በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ድምፅ የመስጠት ሂደት እየተካሄደ እንደሚገኝ ቦርዱ በመረጃው አመልክቷል።