ሁል ሲቲ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመለሰ - ኢዜአ አማርኛ
ሁል ሲቲ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመለሰ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ሻምፒዮምሺፕ የጥሎ ማለፍ የፍጻሜ ጨዋታ ሁል ሲቲ ሚድልስቦሮውን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኦሊ ማክበርኒ በ94ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በጨዋታው ሚድልስቦሮው ብልጫ ቢውስድም ሁል ሲቲ በባከነ ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ግብ አሸናፊ አድርጎታል።
ውጤቱን ተከትሎ ሁል ሲቲ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መመለሱን አረጋግጧል።
ክለቡ ለመጨረሻ ጊዜ በሊጉ ላይ የተወዳደረው እ.አ.አ 2016/17 ነበር።
ሚድልስቦሮው ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ የመመለስ ህልሙ ሳይሳካ ቀርቷል።
ኮቨንተሪ ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን አስቀድመው ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጋቸውን ያረጋገጡ ክለቦች ናቸው።