እኛ ለኢትዮጵያ ብልጽግና በትጋት ስንሰራ፣ ወጣቱ የዚህ ስራ ፍሬ ተቋዳሽ ይሆናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
እኛ ለኢትዮጵያ ብልጽግና በትጋት ስንሰራ፣ ወጣቱ የዚህ ስራ ፍሬ ተቋዳሽ ይሆናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 15/2018 (ኢዜአ) ፦ እኛ ለኢትዮጵያ ብልጽግና በትጋት ስንሰራ፣ ወጣቱ ደግሞ የዚህ ስራ ፍሬ ተቋዳሽ እና የሀገሪቱን ብልጽግና የሚያጣጥም ይሆናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በአሁኑ ወቅት ሀገራቸውን የሚወዱ እና ኢትዮጵያን ከፍ ለማድረግ የሚተጉ ወጣቶችን መመልከት፣ እኛም በበለጠ ትጋት እንድንሰራ ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥርልናል ብለዋል።
" አዶናይ ብርሃነን የመሳሰሉ ወጣቶች እንደ እነ ዲላን ፔጅ ያሉ ታዋቂ የአጫጭር ማኅበራዊ ሚዲያ ዜና አቅራቢዎችን ወደ ሀገራችን በማምጣት የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ ለመገንባት እያከናወኑት ያለው ተግባር የሚበረታታና ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ፣ ወጣቶቹን በርቱ ልንላቸው ይገባል" ሲሉ ገልጸዋል።
ትውልዱ ገብቶታል ያሉት ከንቲባዋ፣ የዛሬው የወጣቶች ድጋፍ እና ተነሳሽነት እጅግ አስደናቂ ነበር ብለዋል።