በዞኑ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
በዞኑ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ
ሰቆጣ፤ ግንቦት 15/2018(ኢዜአ)፦ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ የልማት ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ።
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ ብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍ የአደባባይ ሰልፍ ተካሄዷል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ/ር)፣ የለውጡ መንግስት የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰፋፊ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።
በብሔረሰብ አስተዳደሩም የህዝቡን ጥያቄ መሰረት ያደረጉ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ይህም ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የልማት ስራዎችን በተሻለ ፍጥነትና ጥራት ለማስቀጠል፣ ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ በኩል እያበረከተ ያለውን ሚና አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የዞኑ ነዋሪም ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ፋንታይቱ ካሴ በበኩላቸው፤ በዞኑ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል መርህ በተከናወኑ ስራዎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት በብሔረሰብ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመው፤ ህብረተሰቡ ለአካባቢው ሰላም አበክሮ መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በድጋፍ ሰልፉ የተሳተፉት ወይዘሮ ካሰች ውቡ ለአካባቢያቸው ሰላም መረጋገጥ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ሌላው የሰልፉ ተሳታፊ አቶ ጌታቸው መንግስቴ፣ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።