ቀጥታ፡

በሻምፒዮንስ ሊግ ባየር ሙኒክ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ኢንተር ሚላን ከሊቨርፑል  የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ 

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 30/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የስድስተኛ ጨዋታ መርሃ ግብር ዛሬ ይጀመራል።

ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ ባየር ሙኒክ ከስፖርቲንግ ሊዝበን በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም ይጫወታሉ።

ዘንድሮው በአውሮፓ መድረክ ጥሩ ግስጋሴ እያደረገ የሚገኘው ባየር ሙኒክ በ12 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ስፖርቲንግ ሊዝበን በ10 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። 

ባየር ሙኒክ ካሸነፈ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ ያደርጋል። 

ኢንተር ሚላን ሊቨርፑልን ምሽት አምስት ላይ በጁሴፔ ሚኤዛ ስታዲየም የሚያስተናግድበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የጣልያኑ ቡድን በ12 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። ሊቨርፑል በዘጠኝ ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 

የሶስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ኢንተር ሚላን እና የስድስት ጊዜ የዋንጫው ባለቤት ሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።  

በሌሎች መርሃ ግብሮች አትላንታ ከቼልሲ፣ ባርሴሎና ከኢንትራክት ፍራንክፈርት፣ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከስላቪያ ፕራግ፣ ፒኤስቪ አይንድሆቨን ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ሞናኮ ከጋላታሳራይ እና ዩኒየን ሴይንት ጊሎይስ ከማርሴይ በተመሳሳይ ከምሽቱ አምስት ላይ ይጫወታሉ። 

ካይራት አልማቲ ከኦሎምፒያክስ ከምሽቱ 12 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም