በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ አርባምንጭ ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ አርባምንጭ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 28/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሸገር ከተማ አርባምንጭ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሰርካለም ባሳ፣ ማርታ ወልዴ እና ህይወት ረጉ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ሸገር ከተማ በሊጉ ሰባተኛ ድሉን በማስመዝገብ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ21 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ለሰባተኛ ጊዜ የተሸነፈው አርባምንጭ ከተማ በስምንት ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።
ዛሬ በተደረገ የ11ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ይርጋጨፌ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።