በደቡብ ወሎ ዞን ጊንባ ከተማ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ወሎ ዞን ጊንባ ከተማ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው
ደሴ ፤ህዳር 28/2018(ኢዜአ) ፦በአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የተመራ ልዑክ በደቡብ ወሎ ዞን ጊንባ ከተማ አሥተዳደር በወቅታዊ ክልላዊ እና ሀገራዊ የሰላም እና የልማት ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር እየመከሩ ነው።
በምክክሩ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍሰሀ ደሳለኝ፣ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን፣በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮል እና ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እየተሳተፉ ነው።
በውይይት መድረኩ ከመቅደላ፣ከተንታ እና ከለጋምቦ ወረዳዎች እንዲሁም ከጊንባ እና ከአቀስታ ከተማ አሥተዳደር የተውጣጡ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ይገኛሉ።