ሃዋሳ ከተማ እና መቻል ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ሃዋሳ ከተማ እና መቻል ነጥብ ተጋርተዋል
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 28/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ሃዋሳ ከተማ እና መቻል ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ጋናዊው ኮሊንስ ኮፊ በ38ኛው ደቂቃ ላይ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠራት ጎል መቻል መሪ ሆኗል።
ጌታነህ ከበደ በ68ኛው ደቂቃ ሃዋሳ ከተማን አቻ ያደረገችውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ መቻል እና ሃዋሳ ከተማ በተመሳሳይ 14 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ስድስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን ይዘዋል።