ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከተማ ይርጋጨፌ ቡናን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ አደረገ  

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 28/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ይርጋጨፌ ቡናን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ረፋድ ላይ በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ከአምላክነሽ ሃንቆ በ23ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።

በሊጉ ስምንተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሃዋሳ ከተማ በ25 ነጥብ ደረጃውን ከሶስተኛ ወደ ሁለተኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አዳጊው ይርጋጨፌ ቡና በ10 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም