ብሔራዊ ባንክ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ ከግል ዘርፉ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ብሔራዊ ባንክ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ ከግል ዘርፉ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ ነው
አዲስ አበባ፣ ህዳር 22/2018(ኢዜአ)፦ ብሔራዊ ባንክ ተግዳሮቶችን ለመፍታት፣ ተገዢነትን ለማሻሻል እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ ከግል ዘርፉ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር መመለስ ላይ በሚታዩ ክፍተቶች ዙሪያ ከቡና፣ ሰሊጥ እና ጥራጥሬ ላኪዎች ጋር ተወያይተዋል።
በምክክር መድረኩ ባንኩ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገቢ የመጠበቅ እና የኤክስፖርት ገቢ በወቅቱ እና በግልጸኝነት እንዲመለስ የማድረግ ሃላፊነት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡
ብሔራዊ ባንክ ከሕጋዊ ርምጃ በፊት ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ገንቢ ውይይት ማድረግን እንደሚያስቀድም ተጠቅሷል፡፡
በዚህም ባንኩ ተግዳሮቶችን ለመፍታት፣ ተገዢነትን ለማሻሻል እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ ከግል ዘርፉ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ባንኩ ከዚህ ባለፈም ተጠያቂነትና ኃላፊነት የሚሰማው የወጪ ንግድ ልምዶችን የማበረታታት እና የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱን የማሳደግ ሥራውን እንደሚያጠናክር ነው የተገለጸው ።