ቀጥታ፡

ሶስተኛው የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ህዳር 21/2018(ኢዜአ)፦የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የ2025 የሚዲያ ሽልማት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በመካሄድ ላይ ነው።

የሽልማት ስነ ስርዓቱ “ውጤታማ የአየር ንብረት ዘገባ ደህንነቱ ለተረጋገጠ፣ጠንካራ እና የተረጋጋ ቀጣና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለው።

በመድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ፣ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኢጋድ ቀጣናዊ ሁነቱን ያዘጋጀው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር ሲሆን ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ የሽልማቱ ብቸኛ የሚዲያ አጋር ነው።


 

በመርኃግብር በአፍሪካ ቀንድ ውጤታማ የአየር ንብረት ትርክትን ለቀረጹ ጋዜጠኞች እና የፊልም ባለሙያዎች እውቅና ይሰጣል።

የኢጋድ የሚዲያ ሽልማት ከእ.አ.አ 2023 ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኝ ዓመታዊ ሁነት ሲሆን የ2023 ሽልማት በጅቡቲ የተካሄደ ሲሆን የ2024ቱ ደግሞ በኬንያ ናይሮቢ መካሄዱም ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም