ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ያደረገበት ድል አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ ህዳር 7 /2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልደታ ክፍለ ከተማን 4 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መሳይ ተመስገን ሁለት ግቦችን ከመረብ ላይ ስታሳርፍ ምርቃት ፈለቀ እና እፀገነት ግርማ ቀሪዎችን ጎሎች አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እየቀሩት በ12 ነጥብ ደረጃውን ከአምስተኛ ወደ ሶስተኛ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ልደታ ክፍለ ከተማ በአምስት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በአሁኑ ሰዓት ባህር ዳር ከተማ ከአርባምንጭ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም