ቀጥታ፡

በኮምቦልቻ ለዘመናዊ አገልግሎት እና ለሰው ተኮር ተግባራት የተሰጠው ትኩረት የሚደነቅ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 7/2018(ኢዜአ)፦በኮምቦልቻ ለዘመናዊ አገልግሎት እና ለሰው ተኮር ተግባራት የተሰጠው ትኩረት የሚደነቅ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ዛሬ የኮምቦልቻ ሪጆፖሊታን ከተማ አስተዳደር የዲጂታል አገልግሎትና የዘመናዊ የሥራ ቦታ እድሳትና ሰው ተኮር ተግባራትን መመልከታቸውን አስታውቀዋል። 

የከተማ አስተዳደሩ ህንጻ የስማርት ሲቲ እሴቶችን ባሟላ መልኩ መታደሱን ገልጸዋል። 


 

ህንጻው ዲጅታል አሰራርን ለመተግበር በሚያስችል መልኩ መደራጀቱ አገልግሎትን ለማዘመን አጋዥ አቅም ይፈጥራልም ብለዋል።

በተጨማሪም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከተማዋ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ለሚገኙ ነዋሪዎች ተገንብተው ለነዋሪዎች የተላለፉ መኖሪያ ቤቶችን መመልከታቸውን ጠቁመዋል፡፡


 

የከተማ አስተዳደሩ ባለሀብቶችንና ህብረተሰቡን በማስተባበር ባስገነባቸው ሁለት የመኖሪያ ብሎኮች ለአቅመ ደካሞችና አረጋውያን ደረጃቸውን የጠበቁ ቤቶችን ማስረከቡን ነው የገለፁት።


 

በኮምቦልቻ የጎበኘናቸው የዲጂታል የከተማ አገልግሎት ፕሮጀክትና ሰው ተኮር ተግባራት  በከተሞቻችን እየተገበርናቸው ያሉ የአካታች ልማት ማሳያዎች ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም