ቀጥታ፡

ተቋርጦ የነበረው የቴሌቪዥን ስርጭት ተመለሰ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 5/2018(ኢዜአ)፦ተቋርጦ የነበረው የቴሌቪዥን ስርጭት ተመልሷል።

የሳተላይት አቅራቢ ድርጅት በሆነው SES የቴሌ ፖርት ላይ እስራኤል አካባቢ ባጋጠመው ከፍተኛ የአየር ፀባይ ለውጥ ምክንያት የኃይል መቋረጥ ተፈጥሮ ነበር፡፡

በዚሁ ምክንያት ኢቢሲ ፤የፋና ቴሌቪዥን እና የአብዛኛዎቹ የሀገራችን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ስርጭት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፤ አገልግሎቱን ለመመለስ በተሰራው ሥራ የቴሌቪዥን ስርጭቱ ተመልሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም