በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሸገር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሰርካለም ባሳ እና የድሬዳዋ ከተማዋ ብዙነሽ እሸቱ በራስዋ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
መዓዛ አብደላ ለድሬዳዋ ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።
ድሉን ተከትሎ አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ በ12 ነጥብ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል።
በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በሶስት ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።
የስድስተኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
በተያያዘም ዛሬ በተደረገ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አርባምንጭ ከተማን 5 ለ 1 አሸንፏል።