እስካሁን ከ2ሺህ 96 ቶን በላይ እሸት ቡና ተሰብስቧል - ኢዜአ አማርኛ
እስካሁን ከ2ሺህ 96 ቶን በላይ እሸት ቡና ተሰብስቧል
አዲስ አበባ፤ ህዳር 3/2018(ኢዜአ)፡- በ2018 በጀት ዓመት እስካሁን በተሰራ ስራ 2ሺህ 96 ነጥብ 37 ቶን እሸት ቡና መሰብሰቡን የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
በበጀት ዓመቱ 7ሺህ 880 ቶን እሸት ቡና ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን የመምሪያው ምክትል እና የቡናና ቅመማቅመም ዘርፍ ኃላፊ ከአብነህ ተስፋዬ ለኢዜአ ገልጸዋል።
በዚህም እስካሁን 2ሺህ 96 ነጥብ 37 ቶን እሸት ቡና መሰብሰቡን ገልጸው፤ አሁንም ወደ ማዕከላዊ ገበያ የሚላክ ቡና በተለያዩ ግብይቶች እየተሰበሰበ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል 8 ነጥብ 9 ቶን የታጠበ እንዲሁም 343 ነጥብ 5 ቶን ያልታጠበ የተቀሸረ ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ መላኩን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅትም ብክነት እንዳይኖር የደረሰ ቡና ከስር ከስር በቅንጅት እየተሰበሰበ መሆኑንም አመላክተዋል።